ሴቶች ለምንድን ነዉ አግብተዉ ወደ ሌላ ሰዉ ቤት(ባል ቤተሰብ)የሚሄዱት ?
ምክንያቱም ሴቶች በአንድየ የተባረኩ መላእክት ናቸዉና የራሳቸዉን ቤት በደስታ
ከሞሉ በኋላ የሌሎችን ቤት በደስታ ለማጥለቅለቅ ቤታቸዉን ጥለዉ ይሄዳሉ፡፡
ክብር ለሴቶች!!
የህጻን ልጅ ፎቶ
አንዲት ልጅ ፓርክ ዉስጥ እየተጫወተች ሳለ ቁጥቋጦ ስር ፎቶ ወድቆ ታገኛለች፡፡አንስታ ያዘችዉ፡፡አመታት አለፉ ልጅቱም አድጋ ተዳረች፡፡የሰርጓ እለት ባሏ‹ሁሌም ቦርሳሽ ዉስጥ የማይጠፋዉ የህጻን ልጅ ፎቶ ማን ነዉ? ›ብሎ ጠየቃት፡፡እሷም ‹የመጀመሪያ ፍቅሬ ነዉ› ብላ መለሰችለት፡፡ልጁም ፈገግ አለና ይገርምሻል የ 9 ዓመት ልጅ ሳለሁ ነበር እሱ ፎቶ የጠፋኝ አላት፡