የህጻን ልጅ ፎቶ
አንዲት ልጅ ፓርክ ዉስጥ እየተጫወተች ሳለ ቁጥቋጦ ስር ፎቶ ወድቆ ታገኛለች፡፡አንስታ ያዘችዉ፡፡አመታት አለፉ ልጅቱም አድጋ ተዳረች፡፡የሰርጓ እለት ባሏ‹ሁሌም ቦርሳሽ ዉስጥ የማይጠፋዉ የህጻን ልጅ ፎቶ ማን ነዉ? ›ብሎ ጠየቃት፡፡እሷም ‹የመጀመሪያ ፍቅሬ ነዉ› ብላ መለሰችለት፡፡ልጁም ፈገግ አለና ይገርምሻል የ 9 ዓመት ልጅ ሳለሁ ነበር እሱ ፎቶ የጠፋኝ አላት፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ያያት ፓሪ ላይ ነበር፡፡ልብን ቀጥ የምታረግ ሴት ስለነበረች ሁሉም ወንድ ይከታተላት ነበር፡፡እሱ ግን መደበኛ ሚባል አይነት ሰዉ ስለ ነበር ማንም ሰዉ ትኩረትን አልሰጠዉም ፡፡ዝግጅቱ ሲያበቃ አብረዉ ሻይ ቡና እንዲሉ ግብዣ አቀረበላት፡፡ግብዣዉ ቢያስገርማትም ይሉኝታ ይዟት እሺ በማለት ቃል ገባችለት፡፡ወደ ጥሩ ካፌ አምረተዉ ቡና አዘዙ፡፡በማህላቸዉ ጸጥታ ሰፈነ፡፡ልጁ አንዲት ቃል ትንፍሽ ማለት ፈራ፡፡ሚያረገዉ ነገር ቅጡ ጠፋዉ፡፡ተርበተበተ፡፡ ልጅቱ ሁኔታዉ አልተመቻትም በዉስጧ ምናለ ብሄድበት እያለች ታስብ ነበር ፡፡‹እባክህ ቡናየ ዉስጥ ማደርገዉ ጨዉ ልታመጣልኝ ትችላለህ › ብሎ አስተናጋጁን ጠየቀዉ፡፡ሁሉም ሰዉ በመገረም ይመለከተዉ ጀመር፡፡ፊቱ ቀላ፡፡ቢሆንም ግን አስተናጋጁ ያመጣለትን ጨዉ ቡናዉ ዉስጥ ቀላቅሎ መጠጣት ጀመረ፡፡‹ለምንድን ነዉ ይሄ ልምድ ሊኖርህ የቻለዉ›በማለት በጉጉት ጠየቀችዉ፡፡‹ ልጅ እያለሁ ያደኩበት ስፍራ ባህር ያለበት ነበር ፡፡እኔም በሀሩ አካባቢ አና ዉስጥ መጫወት እወድ ነበር፡፡ሁሌም የበሀሩ ጠዓም ቡና በጨዉ ያለዉን ጣዕም እንዳለዉ አይነት ይሰማኝ ነበር፡፡አሁን ቡና በጨዉ በጠጣሁ ቁጥር ልጅነቴን አስታዉሳለሁ፣የትዉልድ ስፍራየን አስታዉሳለሁ፣የትዉልድ ስፈራየ በጣም ይናፍቀኛል፣እዛዉ እየኖሩ ያሉት ቤተሰቦቼም በጣም ይናፍቁኛል› ብሎ ሲነግራት አይናቹ እንባ አቀረሩ ፡፡ልቧ ተነካ በጥልቅ ተሰማት፡፡ከልቡ የወጣ እዉነተኛ ስሜት ነበር፡፡የትዉልድ ስፍራዉን ናፍቆት ሚናገር ወንድ፤አገርን ሚወድ፣ስለ አገሩ ሚጨነቅ ፣ሃላፊነት ሚሰማዉ ወንድ መሆን አለበት ብላ አሰበች፡፡ከዛም ስለ ራሷ፣ሩቅ ስፍራ ስለሚገኘዉ የሷ የትዉልድ ስፍራ፣ስለ ልጅነቷ፣ስለ ቤተሰቦቿ ማዉራት ጀመረች፡፡የሚገርም ዉይይት ነበር፡፡ የሚያምር ታሪካቸዉ በዚህ መልኩ ተጀመረ፡፡ ከዛን ቀን ጀምሮ መገናኘታቸዉን ቀጠሉ፡፡የሷን መስፈርት የሚያሟላ ሰዉ ሁኖ አገኘችዉ፡፡አዛኝ ልብያለዉ ትዕግስተኛ እና ጠንቃቃ ሰዉ ነበር፡፡ለጥቂት አምልጧት ነበር ለባለጨዉ ቡና ምስጋና ይግባዉና! ቀሪ ታሪኩ ልክ እንደ ሌሎች ምርጥ የፍቅርታሪኮች ነበር፡፡ልእልቷ ልዑሉን አገባችዉ….በደስታ መኖር ጀመሩ...ሁሌም ቡና ባፈላችለት ቁጥር ምን እንደሚወድ ስለምታዉቅ ጨዉ እያረገች ትሰጠዋለች፡፡ከ40ዓመት በኋላ አረፈ፡፡ሂወቱ ከማለፉ በፊት ግን ደብዳቤ ጽፎ አስቀምጦላት ነበር፡፡
ደብዳቤዉ እንዲህ ይላል ‹የኔ ዉድ! ይቅርታ አድርጊልኝ፤እድሜ ልኬን ስለ ዋሸሁሽ ይቅር በይኝ፡፡እያወራሁ ያለሁት በሂወቴ ስለዋሸሁሽ አንድ ዉሸት ብቻ ነዉ፡፡እሱም ስለ ባለ ጨዉ ቡና ነዉ፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ ስንገናኝ ታስታዉሻለሽ በጣም ፈርቸ እየተርበተበትኩ ነበር፡፡ጥቂት ስኳር ነበር የፈለኩት ግን ተሳስቼ ጨዉ አልኩ፡፡በዛን ሰአት ሀሳቤን ለመቀየር በጣም አስቸጋሪ ነበር እና ዝም ብየ ቀጠልኩበት፡፡ የመግባቢያችን ጅማሬ ይሆናል ብየ በፍጹም አላሰብኩም ነበር፡፡እዉነቱን ብዙ ጊዜ ልነግርሽ ፈልጌ ነበር ነገር ግን ያን ለማረግ ፈራሁ፡፡ምንም ነገር ላልዋሽሽ ቃል ገብቸልሽ ስለነበር፤ አሁን እየሞትኩ ስለሆነ ምፈራዉ ነገር የለም፡፡በእዉነቱ ቡና በጨዉ አልወድም እንዴት አይነት መጥፎ ጠዐም መሰለሽ ያለዉ! …ነገር ግን አንቺን ከተዋወኩ ጀምሮ ቡና በጨዉ ስጠጣ ነበር፡፡ይሀንም በማረጌ አንድም ቀን ቅር ብሎኝ አያዉቅም፡፡ላንች ብየ ያደረኩት ነገር አንዱም ቅር አሰኝቶኝ አያዉቅም፡፡በሂወቴ ትልቁ ደስታ አንቺ አጠገቤ መኖርሽ ነዉ፡፡ሂወትን እንደገና መኖር ብችል ካንቺ ጋር መተዋወቅ እና በዘመኔ ሁሉ አብረሽኚ እንድትሆኚ እፈልጋለሁ፡፡ዘላለም ቡና በጨዉ እየጠጣሁም ቢሆን፡፡›
አንብባ ስትጨርስ እንባዋ ደብዳቤዉን አራሰዉ፡፡የሆነ ቀን አንድ ሰዉ ‹ቡና በጨዉ ምን አይነት ጠዐም አለዉ› ብሎ ጠየቃት ‹ጣፋጭ› ብላ መለሰችለት፡፡
ምንጭ-- http://
ይገርማል!
ከወደዱት ላይክ በማድረግ ሸር ያድርጉት፡፡
ፍቅር ይብዛላችሁ!
No comments:
Post a Comment