ስህተት
ከባለቤቴ ጋር ለ10 ዓመታት በትዳር ቆይተናል፡፡ብዙ ተመሳሳይ ፍላጎቶች አሉን፡፡ሁለታችንም ብዙ ጓደኞች አሉን፡፡አብረን ግዜ ማሳለፍ እንወዳለን፡፡ባል እና ሚስት ከአንድ ወንዝ ይቀዳሉ ሚለዉ አባባል ለኛ ሚስማማ ይመስለኛል፡፡ሁለታችንም ቤት መዋል ስለምንወድ ጓደኞቻችን እኛ ቤት መጠዉ መዝናናት ይመርጣሉ፡፡
ረጅሙን ታሪክ ለማሳጠር ባላወኩት ምክንያት ዉዱ ባለቤቴ ከምወዳት ባለንጀራየ ጋር እየማገጠ መሆኑን ጠረጠርኩ፡፡በርግጥ አብረዉ ተኝተዉ አላገኘኋቸዉም፡፡አለ አደል ለረጅም ጊዜ የምታዉቁት ሰዉ እየተቀየረባችሁ ሲመጣ ፤እጅ ከፈንጅ ባልይዛቸዉም በሁለታቸዉ መሀል የሆነ ነገር እየተካሄደ እንዳለ ተሰማኝ ፡፡
በሂወቴ ትልቅ ሚና ባላቸዉ ሁለቱ ሰወች እንደተካድኩ ተሰማኝ፡፡ አሳበደኝ፡፡ነገሮችን ግልፅ ለማድረግ ሁለቱንም ፊት ለፊት እንደመጋፈጥ ሁሉንም ነገር በሆዴ አምቄ መብሰክሰክ እና በቅናት መቃጠልን መረጥኩ፡፡
እራሴን ተጎጂ ማድረጌ የመረጥኩት ቢሆንም ቀጥሎ የፈፀምኩት ግን በሂወቴ ከፈፀምኳቸዉ ስህተቶች ትልቁን ስህተት ነበር፡፡ባለቤቴን መጉዳት ፈለኩ እና ከጓደኛዉ ጋር መሽኮርመም ጀመርኩ፡፡በርግጥ ሰዉየዉ ጓደኛዉ ባይባልም ለተወሰነግዜ ይተዋወቃሉ፡፡ይህ ሰዉ ይወደኛል ያዉ ወንድ ልጅ ሲወድሽ ያስታዉቅ የለ፡፡
አንድ ቀን ሰዉየዉን ቤት እንዲመጣ ጋበዝኩት፡፡ከቆይታ በኋላ ሰለ ባሌ ጭካኔ ፣ ታማኝ አለመሆን እና እንዴት እነደተጎዳሁ ማማረር ጀመርኩ ፡፡ሰዉየዉ አማራጭ እንዳይኖረዉ ራሴን ነፃ ማድረጌ ነበር፡፡ ያን ምሽት ከሰዉየዉ ጋር አንሶላ ተጋፈፍን፡፡በማግስቱ ከእንቅልፌ ስነቃ ከባድ ስህተት እን ደሰራሁ ተሰማኝ፡፡ምን ይሀ ብቻ የባሰዉ ነገር ገና መች ተከሰተና
በቀጣዩ ወር ሁለት ነገሮጀ በአንድ ላይ ተከሰቱ፡፡አንደኛዉ ያቺ በባሌ የጠረጠርኳት ባለንጀራየ ሰረግ መጠራቴ ሲሆን ሁለተኛዉ እርጉዝ መሆኔን ማወቄ ነዉ፡፡ለባሌም ይሁን ለዛኛዉ ሰዉየ አልነገርኳቸዉም፡፡የፀነስኩት ከማን እንደሆነ ባለማወቄ ተሸማቅቄአለሁ፡፡ማረገዉ ጨንቆኛል፡፡ባለቤቴ እነደሚወደኝ አዉቃለሁ፡፡ እኔም አወደዋለሁ ግንእዉነታዉን ከነገርኩት ትዳራችን ምስቅልቅሉ እንደሚወጣ አዉቃለሁ፡፡ የሱ ላይሆን የሚቸለዉን ልጅ ሲያሳድግ ዝም ብሎ የማቱ ድፍረት ይኖረኝ ይሆን?
ምን ማረግ እንዳለብኝ አላዉቅም፡በርግጠኝነት የማዉቀዉ አንድ ነገር ብቻ ነዉ፡፡ እሱም ሂወቴ የተበላሸ መሆኑን ብቻ ነዉ፡፡
ፀሀፊዋ

No comments:
Post a Comment