Wednesday, October 18, 2017

አስገራሚ የፍቅር ታሪክ

ቆንጆ የፍቅር ታሪክ

https://yefikir.blogspot.com.es/2017/10/blog-post_23.html ልጁ በ ኦንላይን ከ ሴት ጋር ይተዋወቃል ፡፡ቀስ በቀስ ማዉራት ይጀምራሉ፡፡ሁሌም ኦንላይን ተገናኝቶ ማዉራት የዘወትር ተግባራቸዉ ሆነ እና ጥሩ ጓደኛሞች ሆኑ፡፡ከጥቂት ወራት በኋላ በፍቅር ወደቁ እና ፍቅራቸዉን ተገላልፀዉ ለጥቂት ሳምንታት በደስታ አሳለፉ፡፡
ባልታወቀ ምክንያት ልጅቱ መልእክት መላክ አቆመች፡፡ልጁ ጠበቀ ጠበቀ ወፍ የለም፡፡ ሳምንታት አለፉ፡፡ ኮምፒተሩን አፍጥጦ እያየ መጠባበቁን ቀጠለ ጠብ ያለ ነገር የለም፡፡አምኖ መቀበል ባይፈልግም የሆነ አደጋ እንደደረሰባት ይሰማዋል ፡፡ከብዙ ጊዜ በኋላ የሱ እና የልጅቱ ግንኙነት እንዳበቃለት አምኖ ተቀበለ፡፡ነገር ግን ልቡ ተሰበረ ሁሌም አልጋዉ ላይ ከልጅቱ የተላከለትን የቆዩ መልእክቶች እያነበበ ያለቅሳል::በጣም ዉሰጡ ተጎዳ፡፡
ከጥቂት አመታት በኋላ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ መማር ይጀምራል፡፡በፍቀር የተሰበረዉ ልቡ ሴት ለምኔ አሻፈረኝ ስላለ ከሌላ ሴት ጋር ለመተዋወቅ ሳይሞክር ሂወቱን ቀጠለ፡፡ይሁን እና በአቋሙ እንዳይፀና የምታረገዉ ልጅ በዩኒቨርሲቲዉ ዉስጥ ተከሰተች፡፡ ሊገልፀዉ ማይችለዉ መግነጢሳዊ ሃይል ወደ ልጅቱ እንዲሳብ ያደርገዉ ጀመር፡፡እንደምንም ብሎ ተጠጋት እና እንደወደዳት ገለፀላት ወዲያያዉ ጥያቄዉን ዉድቅ አደረገችበት፡፡
ልጁ፡ ይቅርታ እናቱ በጣም ወድጀሻለሁ፡፡
ልጅት፡ ይቅርታ አባቱ እኔ ደሞ ከሌላ ሰዉ ጋር በፍቅር ወድቄአለሁ ፡፡
ልጁ፡ እሽ እናቱ፡፡ እና በሌላ ሰዉ ተይዘሻል ማለት ነዉ?
ልጅት፡ እንደዛ እንኳ አደለም፡፡ክሶስት አመት በፊት የዚህ አካባቢ ልጅ ከሆነ ሰዉ ጋር በ ፍቅር ወደኩ፡፡እና በሆነ አጋጣሚ ልጁን ተዉኩት እና ዩኒቨርሲቲን ምክንያት በማድረግ እሱን ፍለጋ ነዉ የመጣሁት፡፡
ልጁ፡ አይገርምም እኔም ከአንቺ ጋር ሚመሳሰል ታሪክ አሳልፌአለሁ!
ልጅት ፡ ልጅቱ ማን ነበር ስሟ ?
ልጁ፡ ሀ(የልጅቱን ደብተረር ሲያይ ሀ ሚል ስም ተፅፎበታል)
ሁለቱም ተቃቅፈዉ ስቅስቅ ብለዉ ማልቀስ ጀመሩ፡፡
ልጁ፡ ለምን ግን ተዉሽኝ? ለምን መፃፍ አቆምሽ?
ልጅት፡ የመኪና አደጋ አጋጥሞኝ ለአመታት ሰዉነቴ ሁሉ ሽባ ሁኖ ነበር፡፡ከ6 ወር በፊት ነዉ የተሸለኝ፡፡መግባት ምትፈልገዉ እዚህ ዩንቨርሲቲ መሆኑን ነገረህኝ ስለ ነበር ሲሻለኝ አንተን ለማገኘት ብየ እዚህ ዩኒቨርሲቲ አመለከትኩ፡፡
ታሪኩን ከወደዳችሁት ሸር አርጉት ፡፡
ፍቅር ይብዛላችሁ!

መጋባት አትችሉም በመባላቸዉ ራሳቸዉን ያጠፉት የዘመኑ ሮሚዮ እና ጁልየት

https://yefikir.blogspot.com.es/2017/10/blog-post_97.html
መጋባት አትችሉም በመባላቸዉ ራሳቸዉን ያጠፉት የዘመኑ ሮሚዮ እና ጁልየት

ህንድ ጋዜጣ ላይ ተቀብሮ የኖረ ታሪክ ነዉ፡፡በ2009 ሁለት እድለ ቢስ ህንዳዉያን ፍቅረኞች በሃገር ሽማግሌወች መጋባት አትችሉም በመባላቸዉ ምክንያት እራሳቸዉን አጥፍተዋል፡፡

አምሪን ሙስሊም ባለቤቷ ደሞ የሂንዱ እምንት ተከታይ ነበር፡፡ለ አካባቢዉ ሰወች የሁለቱ ጋብቻ ተቀባይነት ያልነበረዉ ጥምረት ነበር፡፡በዚህ ምክንያት ሁለቱ ፍቅረኞች መርዝ ጠጥተዉ እራሳቸዉን አጥፍተዋል፡፡ፖሊስ ያሀገር ሽማግሌወችን ራስ ማጥፋትን በማበረታታት እና ማገዝ በሚል ክስ ከሷቸዋል፡፡

ፍቅር እራሱን እንጂ ሌላ ምንም አይሰጥም

https://yefikir.blogspot.com.es/2017/10/blog-post_46.html
ፍቅር እራሱን እንጂ ሌላ ምንም አይሰጥም
ከራሱ እንጂ ከሌላ ከማንም አይቀበልም፡፡
-ከሀሊል ጅብራን

ፍቅር በአይኖቹ ጥቅሻ በጠራችሁ ግዜ ምንም እንኳ መንገዶቹ አስቸጋሪ እና አቀበት ቢሆኑም ተከተሉት፡፡
ክንፎቹ ሲያቅፏችሁም ተሸጎጡበት፡፡ በላባወቹ መሀል የተደበቁት ሰይፎች ቢያቆስሏችሁም ወደኋላ አታፈግፍጉ፡፡
ሲያነጋግራችሁም እመኑት፡፡ ድምጹ የሰሜን ኃይለኛ አወሎ ንፋስ፤
የአትክልት ስፍራን እንደሚያወድም፤ ሁሉ ህልሞቻችሁን ቢበታትንባችሁም እሱን ከማመን አታመንቱ፡፡
ፍቅር ዘዉድ የሚደፋባችሁን ያህል ይሰቅላችሁም ይሆናል ፡፡የሚያሳድጋችሁን ያህልም ይከረክማችኋል፡፡
እንደበቆሎ ክምር ወደራሱ ይሰበስባችኋል ፡፡እርቃናችሁን ሊያስቀራችሁ ይወቃችኋል፡
ከላንፋችሁ ሊያላቅቃችሁ ይነፋችኋል፡፡ነጭ ዱቄት እስክትሆኑ ድረስ ይፈጫቻኋል፡፡
እስክትለወጡም ድረስ ያቦካችኋል፡፡ ከዚያ ለእግዝአብሄር ቅዱስ ድግስ፤ የምትባረኩ ቅዱስ ዳቦዎች ትሆኑ ዘንድ
ወደ ተቀደሰዉ እሳቱ ይጨምራችኋል፡፡
ይሁን እና ፍርሃት አድሮባችሁ የፍቅርን ሰላም እና ደስታ ብቻ የምትሹ ከሆነ
እርቃናችሁን ሸፍናችሁ፣ከፍቅር የመዉቂያ አዉድማ ወጥታችሁ ብትሄዱ ይሻላችኋል፡፡
ወደዚያ የሄዳችሁበት ወቅት የማይፈራረቅበት ፣ወቅት-አልባ አለም ዉስጥ ትሰቃላችሁ፡፡
ነገር ግን ሳቃችሁን ሁሉ አትስቁትም፡፡ታለቅሳላችሁ ነገር ግን እንባችሁን ሁሉ አታፈሱትም፡፡
ፍቅር እራሱን እንጂ ሌላ ምንም አይሰጥም፣
ከራሱ እንጂ ከሌላ ከማንም አይቀበልም ፍቅር ለፍቅር በቂ ነዉእና፡፡
-ከሀሊል ጅብራን

ልስምሽ አደለም ከንፈሮችሽን ሚስጥር ልነግራቸዉ ነዉ፡፡

ለ ስምንት አመታት ጓደኛዉን በጀርባዉ ያዘለዉ ታዳጊ

ለ ስምንት አመታት ጓደኛዉን በጀርባዉ ያዘለዉ ታዳጊ

ፍቅር በጥንዶች ብቻ ሳይሆን በጓደኞች መካከልም ያለ የነበረ እና የሚኖር ነዉ፡፡በህቤ ቻይና የሚኖር ሉ ሺ ቺንግ የተባለ የ16 አመት ታዳጊ በህመም ምክንት መራመድ የማይችለዉን ሉ ሻዉ የተባለዉን ጓደኛዉ ለስምንት አመታት በጀርባዉ አዝሎ ከትምህርት ቤት ወደ ቤት እያመላለሰዉ ይገኛል፡፡
የዛሬ ስምንት አመት ዝናባማ በሆነ እለት የ ሉ ሻዉ እናት ልጇን ለመዉሰድ ሳትመጣ ትቀራለች፡፡ መራመድ የማይሆንለት ሉ ሻዉ
በጣም ተቸገረ፡፡ ይህንን ችግር ያየዉ ሉ ሺ ቺንግ ምንም እንኳን ሉ ሻዉ ከሱ የገዘፈ ቢሆንም አዝሎ ቤቱ ሊያደርሰዉ ይወስናል፡፡ ተሳክቶለትም አደረሰዉ፡፡ከዛን እለት ጀምሮ ሉ ሺ ቺንግ ያለማቋረጥ ጓደኛዉን ወደ ትምህርት ቤት የማድረስ ተግባሩነረ ቀጠለበት፡፡
ይህንን ተግባር በመፈጸሙ እራሱን ለመኮፈስ ወይም ሰዉ እንዲያደንቀዉ አልፈለገም፡፡ሌላዉ ይቅር እና ቤተሰቦቹ እንኳን ያወቁት ከ አራት አመታት በኋላ ነበር፡፡ሉ ሻዉ በማስታወሻዉ ላይ የጓደኛዉ እገዛ በጭጋግ ተሸፍኖ የነበረዉ ሂወቱ ላይ ብርሀን እንደለኮሰበት ጽፏል፡፡

ምርጥ የፍቅር ታሪክ

https://yefikir.blogspot.com.es/2017/10/blog-post_18.html
ምርጥ የፍቅር ታሪክ

ለመጀመሪያ ጊዜ ያያት ፓሪ ላይ ነበር፡፡ልብን ቀጥ የምታረግ ሴት ስለነበረች ሁሉም ወንድ ይከታተላት ነበር፡፡እሱ ግን መደበኛ ሚባል አይነት ሰዉ ስለ ነበር ማንም ሰዉ ትኩረትን አልሰጠዉም ፡፡ዝግጅቱ ሲያበቃ አብረዉ ሻይ ቡና እንዲሉ ግብዣ አቀረበላት፡፡ግብዣዉ ቢያስገርማትም ይሉኝታ ይዟት እሺ በማለት ቃል ገባችለት፡፡ወደ ጥሩ ካፌ አምረተዉ ቡና አዘዙ፡፡በማህላቸዉ ጸጥታ ሰፈነ፡፡ልጁ አንዲት ቃል ትንፍሽ ማለት ፈራ፡፡ሚያረገዉ ነገር ቅጡ ጠፋዉ፡፡ተርበተበተ፡፡ ልጅቱ ሁኔታዉ አልተመቻትም በዉስጧ ምናለ ብሄድበት እያለች ታስብ ነበር ፡፡‹እባክህ ቡናየ ዉስጥ ማደርገዉ ጨዉ ልታመጣልኝ ትችላለህ › ብሎ አስተናጋጁን ጠየቀዉ፡፡ሁሉም ሰዉ በመገረም ይመለከተዉ ጀመር፡፡ፊቱ ቀላ፡፡ቢሆንም ግን አስተናጋጁ ያመጣለትን ጨዉ ቡናዉ ዉስጥ ቀላቅሎ መጠጣት ጀመረ፡፡‹ለምንድን ነዉ ይሄ ልምድ ሊኖርህ የቻለዉ›በማለት በጉጉት ጠየቀችዉ፡፡‹ ልጅ እያለሁ ያደኩበት ስፍራ ባህር ያለበት ነበር ፡፡እኔም በሀሩ አካባቢ አና ዉስጥ መጫወት እወድ ነበር፡፡ሁሌም የበሀሩ ጠዓም ቡና በጨዉ ያለዉን ጣዕም እንዳለዉ አይነት ይሰማኝ ነበር፡፡አሁን ቡና በጨዉ በጠጣሁ ቁጥር ልጅነቴን አስታዉሳለሁ፣የትዉልድ ስፍራየን አስታዉሳለሁ፣የትዉልድ ስፈራየ በጣም ይናፍቀኛል፣እዛዉ እየኖሩ ያሉት ቤተሰቦቼም በጣም ይናፍቁኛል› ብሎ ሲነግራት አይናቹ እንባ አቀረሩ ፡፡ልቧ ተነካ በጥልቅ ተሰማት፡፡ከልቡ የወጣ እዉነተኛ ስሜት ነበር፡፡የትዉልድ ስፍራዉን ናፍቆት ሚናገር ወንድ፤አገርን ሚወድ፣ስለ አገሩ ሚጨነቅ ፣ሃላፊነት ሚሰማዉ ወንድ መሆን አለበት ብላ አሰበች፡፡ከዛም ስለ ራሷ፣ሩቅ ስፍራ ስለሚገኘዉ የሷ የትዉልድ ስፍራ፣ስለ ልጅነቷ፣ስለ ቤተሰቦቿ ማዉራት ጀመረች፡፡የሚገርም ዉይይት ነበር፡፡ የሚያምር ታሪካቸዉ በዚህ መልኩ ተጀመረ፡፡ ከዛን ቀን ጀምሮ መገናኘታቸዉን ቀጠሉ፡፡የሷን መስፈርት የሚያሟላ ሰዉ ሁኖ አገኘችዉ፡፡አዛኝ ልብያለዉ ትዕግስተኛ እና ጠንቃቃ ሰዉ ነበር፡፡ለጥቂት አምልጧት ነበር ለባለጨዉ ቡና ምስጋና ይግባዉና! ቀሪ ታሪኩ ልክ እንደ ሌሎች ምርጥ የፍቅርታሪኮች ነበር፡፡ልእልቷ ልዑሉን አገባችዉ….በደስታ መኖር ጀመሩ...ሁሌም ቡና ባፈላችለት ቁጥር ምን እንደሚወድ ስለምታዉቅ ጨዉ እያረገች ትሰጠዋለች፡፡ከ40ዓመት በኋላ አረፈ፡፡ሂወቱ ከማለፉ በፊት ግን ደብዳቤ ጽፎ አስቀምጦላት ነበር፡፡
ደብዳቤዉ እንዲህ ይላል ‹የኔ ዉድ! ይቅርታ አድርጊልኝ፤እድሜ ልኬን ስለ ዋሸሁሽ ይቅር በይኝ፡፡እያወራሁ ያለሁት በሂወቴ ስለዋሸሁሽ አንድ ዉሸት ብቻ ነዉ፡፡እሱም ስለ ባለ ጨዉ ቡና ነዉ፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ ስንገናኝ ታስታዉሻለሽ በጣም ፈርቸ እየተርበተበትኩ ነበር፡፡ጥቂት ስኳር ነበር የፈለኩት ግን ተሳስቼ ጨዉ አልኩ፡፡በዛን ሰአት ሀሳቤን ለመቀየር በጣም አስቸጋሪ ነበር እና ዝም ብየ ቀጠልኩበት፡፡ የመግባቢያችን ጅማሬ ይሆናል ብየ በፍጹም አላሰብኩም ነበር፡፡እዉነቱን ብዙ ጊዜ ልነግርሽ ፈልጌ ነበር ነገር ግን ያን ለማረግ ፈራሁ፡፡ምንም ነገር ላልዋሽሽ ቃል ገብቸልሽ ስለነበር፤ አሁን እየሞትኩ ስለሆነ ምፈራዉ ነገር የለም፡፡በእዉነቱ ቡና በጨዉ አልወድም እንዴት አይነት መጥፎ ጠዐም መሰለሽ ያለዉ! …ነገር ግን አንቺን ከተዋወኩ ጀምሮ ቡና በጨዉ ስጠጣ ነበር፡፡ይሀንም በማረጌ አንድም ቀን ቅር ብሎኝ አያዉቅም፡፡ላንች ብየ ያደረኩት ነገር አንዱም ቅር አሰኝቶኝ አያዉቅም፡፡በሂወቴ ትልቁ ደስታ አንቺ አጠገቤ መኖርሽ ነዉ፡፡ሂወትን እንደገና መኖር ብችል ካንቺ ጋር መተዋወቅ እና በዘመኔ ሁሉ አብረሽኚ እንድትሆኚ እፈልጋለሁ፡፡ዘላለም ቡና በጨዉ እየጠጣሁም ቢሆን፡፡›
አንብባ ስትጨርስ እንባዋ ደብዳቤዉን አራሰዉ፡፡የሆነ ቀን አንድ ሰዉ ‹ቡና በጨዉ ምን አይነት ጠዐም አለዉ› ብሎ ጠየቃት ‹ጣፋጭ› ብላ መለሰችለት፡፡
ምንጭ-- http://storiesoftruelove.blogspot.com/
ይገርማል!
ከወደዱት ላይክ በማድረግ ሸር ያድርጉት፡፡
ፍቅር ይብዛላችሁ!